በ9ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ክሪስታል ፓለስን 1 ለ 0 አሸንፏል።
በኢምሬትስ በተደረገው ጨዋታ ኤቤሬቺ ኤዜ የቀድሞ ክለቡ ላይ የማሸነፊያዋን ግብ አስቆጥሯል።
እንግሊዛዊው ኤቤሬቺ ኤዜ በፕሪሚየር ሊጉ ለአርሰናል የመጀመርያ ግቡን ባስቆጠረበት ጨዋታ መድፈኞቹ በሊጉ 4ኛ ተከታታይ ድላቸውን አስመዝግበዋል።
አርሰናል ሊጉን በ22 ነጥብ እየመራ ሲሆን ከተከታዩ ቦርንማውዝ ያለው የነጥብ ልዩነትም አራት ነው።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ካደረጋቸው ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በስድስቱ መረቡን ሳያስደፍር ወጥቷል።
ማንችስተር ሲቲ በአስቶን ቪላ 1 ለ 0 ተሸንፏል። በቪላ ፓርክ በተደረገው ጨዋታ ማቲ ካሽ የአስቶን ቪላን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።
በሌሎች ጨዋታዎች ቦርንማውዝ ኖቲንግሀም ፎረስትን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ ዎልቭስ በበርንሌይ 3 ለ 2 ተሸንፏል።
በአንተነህ ሲሳይ