በ10ኛ ሳምንት የስፔን ላሊጋ ሪያል ማድሪድ ከ ባርሴሎና የተገናኙበት ኤል ክላሲኮ በማድሪድ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
በሳንቲያጎ ቤርናቡ በተደረገው ጨዋታ ኬይሊያን ምባፔ እና ጁድ ቢሊንግሀም የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ፈረንሳዊው አጥቂ ተጫማሪ ግብ የሚያስቆጥርበትን ፍጹም ቅጣት ምት ቢያገኝም ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ፈርሚን ሎፔዝ የባርሴሎናን አንድ ግብ አስቆጥሯል።
በውድድር ዓመቱ 9ኛ ድሉን ያስመዘገበው ሪያል ማድሪድ ሊጉን በ27 ነጥብ እየመራ ሲሆን ከተከታዩ ባርሴሎና ያለውን የነጥብ ልዩነትም ወደ አምስት አስፍቷል።