Search

2ኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጫወታዎች ውድድር ተጀመረ

ቅዳሜ ጥቅምት 15, 2018 49

2ኛውን የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጫወታዎች ውድድር ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ ስታዲየም በድምቀት ተጀምሯል።
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ "አዲስ አበባ ይህንን ውድድር በማስተናገዷ ደስታ ይሰማናል" ብለዋል።
የአዲስ አበባ የስፖርት ቤተሰብ በውድድሩ ስፍራዎች በመታደም የነገ ተተኪ ስፖርተኞችን እንዲደግፍ እና እንዲያበረታታም ከንቲባዋ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።