ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርባ ምንጭ ከተማ በ52 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈውን የኩሪፍቱ ሪዞርት እና ስፓ ዛሬ ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት፤ "አርባ ምንጭ፤ የልማት ምንጭነቷ እየጎመራ ቀጥሏል!" ብለዋል፡፡
ዛሬ የጎበኙት የኩሪፍቱ ሪዞርት እና ስፓ 53 ቅንጡ ቪላዎችን ያካተተ ሲሆን፤ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ጠቅሰዋል።
አክለውም "መሰል ኢንቨስትመንቶች የመደመር መንግሥት የገነባቸውን መሠረተ ልማቶች ተከትሎ የግሉ ዘርፍ ማበርከት የሚችለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው" በማለት የግሉን ዘርፍ የቱሪዝም ተሳትፎ አድንቀዋል።
የሀገራችንን የቱሪዝም አቅም ወደ ላቀ ምዕራፍ በሚያሸጋግሩ መሰል ታላላቅ ፕሮጀክቶች ላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች በስፋት እንዲሰማሩና መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡