Search

አንጋፋዋ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

እሑድ ሰኔ 28, 2018 196

በባህል ሙዚቃ ዜማዎቿ ከፍተኛ አድናቆትን ያገኘችው ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

ድምፃዊት ራሔል ባጋጠማት የጤና እክል ሕክምና እየተከታተለች መቆየቷን ኢቢሲ ከቤተሰቦቿ አረጋግጧል።

ራሔል ዮሐንስ በግሏ እና ከተለያዩ ድምፃውያን ጋር በመሆን በርካታ ተወዳጅነትን ያገኙ ሙዚቃዎች ሠርታለች።

በሙዚቃዎቿ ከድምፃዊነት ባለፈ፣ በአንዳንዶቹ ላይ በግጥም እና በዜማ ድርሰትም አስተዋፅኦ ታደርግ ነበር።

ራሔል ዮሐንስ ከሠራቻቸው ሙዚቃዎቿ መካከል "ኢትዮጵያ" "አራዳ" "እንደ ኢየሩሳሌም" "ትዝታ" "አንቺ ባለድሪ" እና "አየር ኃይላችን" የመሳሰሉት ተወዳጅነት አግኝተውላታል።

ኢቢሲ ለአርቲስቷ ቤተሰቦች እና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል።