Search

የሐረሪ ባህልና ስፖርት ፌስቲቫል በአሜሪካዋ ሜምፊስ የከተማዋ በዓል ሆኖ እንዲከበር ተወሰነ

እሑድ ሰኔ 28, 2018 100

በአሜሪካዋ ሜምፊስ ከተማ የሐረሪ ባህልና ስፖርት ፌስቲቫል የከተማዋ በዓል ሆኖ እንዲከበር የከተማው ምክር ቤት ባካሄደው ጉባኤ መወሰኑ ተገለጸ።

በከተማዋ የሚኖሩ የሐረሪ ማኅበረሰብ በየዓመቱ የሚያከብሩት የስፖርትና ባህል ፌስቲቫል አከባበር ዕውቅና ማግኘቱ ባህሎቻቸውን፣ ታሪኮቻቸውንና እሴቶቻቸውን ለሌላው ማኅበረሰብ በላቀ ደረጃ ለማስተዋወቅ እንደሚያስችል ተጠቅሷል።

ዕውቅናው በተለያዩ ዓለማት ለሚገኙ የሐረሪ ማኅበረሰብ ትልቅ ኩራት ከመሆኑም ባሻገር ጥንታዊ ባህሎቻቸውን ጠብቀው ለማቆየትና ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ትልቅ መነሳሳት የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።

የከተማዋ ምክር ቤት የሰጠው እውቅናም ከተማዋ ለባህል ብዝኃነት፣ ለሕዝቦች የእርስ በእርስ ትውውቅና ትስስር እንዲጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ተመላክቷል።

እንዲሁም በሜምፊስና በሐረር ከተሞች መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።

በዓሉ በየዓመቱ በፈረንጆቹ ጁላይ 1 ቀን እንዲከበር ምክር ቤት በአዋጅ መደንገጉም ተገልጿል።