Search

የዘንድሮው የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ ሲዳማ ቡና ዋንጫውን ተረከበ

እሑድ ሰኔ 28, 2018 374

የ2018ቱ የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በይፋ ተጠናቅቋል።

በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሻምፒዮኑ ሲዳማ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ያደረጉት ጨዋታ፣ በኢትዮ ኤሌክትሪክ 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ አቤል ሀብታሙ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።

ከ38 ሳምንታት የሊጉ መርሐ ግብሮች 68 ነጥብ በመሰብሰብ የ2018ቱን የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ያነሣው ሲዳማ ቡና፣ በቀጣዩ ዓመት በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵያን ወክሎ ተሳታፊ ይሆናል።

ዛሬም የዓመቱ ሻምፒዮን የሆነበትን የክብር ዋንጫ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ከክብር እንግዶች እጅ ተቀብሏል።

በእድሪስ አሕመድ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: