Search

ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ በመግዛት አቅም ተመጣጣኝነት ቀዳሚ መሆኗን አይኤምኤፍ ገለፀ

ሰኞ ሰኔ 29, 2018 53

ኢትዮጵያ በመግዛት አቅም ተመጣጣኝነት (Purchasing Power Parity - PPP) ስሌት ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ መሆኗን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) አስታወቀ።

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ባወጣው ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ በዚሁ የመግዛት አቅም ተመጣጣኝነት ሚዛን 558 ነጥብ 93 ቢሊየን ዶላር የሚያህል ግዙፍ ዓመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP-PPP) ማስመዝገቧን ጠቅሷል፡፡

በዚህም ኢትዮጵያ ከኬንያ እና ታንዛኒያ በመቅደም ከምስራቅ አፍሪካ በአንደኝነት እንድትቀመጥ አስችሏታል።

እነዚህ ሦስቱ ሀገራት (ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ) በጋራ 1 ነጥብ 35 ትሪሊየን ዶላር ዓመታዊ የመግዛት አቅም ተመጣጣኝነት ጥቅል አቅም ማስመዘገባቸውን የአይኤምኤፍ ሪፖርት አመልክቷል፡፡

ይህም ከደረጃ 4 እስከ 19 ላይ የሚገኙ በርካታ የቀጠናው ሀገራት በድምሩ ካስመዘገቡት የኢኮኖሚ አቅም የተሻለ ሆኖ መገኘቱን የሪፖርቱ ትንታኔ አመልክቷል።