Search

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሚዛን አማን ከተማ የቅድመ ምረቃ በረራ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

ረቡዕ ሐምሌ 01, 2018 146

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሚዛን አማን ከተማ ሳምንታዊ የቅድመ ምረቃ በረራዎችን ሊያስጀምር መሆኑን አስታውቋል።

አየር መንገዱ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ ወደ ከተማዋ በሳምንት ሦስት ቀናትን ያማከሉ የበረራ መርሃ ግብሮች የሚከናወኑ ይሆናል።

ይህ አዲስ የቅድመ ምረቃ በረራ መጀመሩ ወደ አካባቢው ለሚጓዙ መንገደኞች የተሻለ የምቾት እና የትራንስፖርት አማራጭ የሚፈጥር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ደንበኞች ከወዲሁ የጉዞ ትኬታቸውን በመቁረጥ መስተንግዶ ማግኘት እንደሚችሉ አየር መንገዱ አስታውቋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: