Search

ከ16 ዓመታት በኋላ የተደገመው ታሪክ፤ ላ ሮሃ የዓለም ሻምፒዮን

ሰኞ ሐምሌ 13, 2018 98

ከአስራ ስድስት ዓመታት በፊት በጆሀንሰበርግ ሰማይ ስር የተጻፈው ያ ውብ የታሪክ ምዕራፍ በኒውጀርሲው የሜትላይፍ ስታዲየም በድጋሚ ሲከፈት፣ እግር ኳስ ፍትህ ያሰፈነች መሆኑን በድጋሚ አረጋግጣለች።

“ስፔን ኳስ ለመጫወት ወደ ሜዳ ገባች፣ አርጀንቲና ደግሞ እነርሱን ለማቆም” በሚለው ጠንካራ እውነታ የተመራው የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ፣ የወቅቱ የአውሮፓ ሻምፒዮን ስፔን በአርጀንቲና ላይ ፍጹም የበላይነትን ተቀዳጅታ የዓለም ሻምፒዮን የሆነችበትን ታሪካዊ ምዕራፍ አብስሯል።

ፌራን ቶሬስ በጨዋታው ጀግና በመሆን ከ16 ዓመታት በፊት አንድሬስ ኢኒየሽታ የሰራውን ታሪክ በድጋሚ ደግሞታል።

ጨዋታው ሲጀመር አንስቶ እስከ መጠናቀቁ ድረስ ስፔን ሙሉ የጨዋታውን ቁጥጥር በመውሰድ አርጀንቲናዎችን ኳስ እግራቸው ስር እንዳይቆይ አድርጋለች።

በአንፃሩ ሊዮኔል ሜሲ በውስን አጋጣሚዎች ካልሆነ በቀር አብዛኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ከዕይታ ርቆ ከእንቅስቃሴ ተገድቦ ቆይቷል።

የአርጀንቲና የኃይል አጨዋወት ፍላጎት በኤንዞ ፈርናንዴዝ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበት የተገለጸ ሲሆን፣ ተጫዋቾቹ የፈጸሟቸው 25 ጥፋቶችም የጨዋታውን ውጥረት የሚያመላክቱ ነበሩ።

ቁጥራዊ መረጃዎች እንደሚነግሩን ስፔን በተጋጣሚዋ ሦስተኛ የሜዳ ክፍል 235 የተሳኩ የኳስ ንክኪዎች ሲኖሯት፣ አርጀንቲና ይህ የተሳካላት በ35 አጋጣሚዎች ብቻ ነው።

በ38 ተከታታይ ጨዋታዎች ያልተሸነፈው እና በዚህ ዓለም ዋንጫ አንድ ግብ ብቻ የተቆጠረበት የስፔን ስብስብ፣ ወጀቡ ሳይረታው እና ግርግር ሳይገታው በጸጥታ ወደ ከፍታው ወጥቷል።

ከኮከብ ግብ አስቆጣሪነቱ ውጪ ያሉትን ሁሉንም ግዙፍ ሽልማቶች የወሰደችው ስፔን፣ ፓብሎ ኩባርሲን በወጣት ዘርፍ፣ ኡናይ ሲሞንን በግብ ጠባቂ፣ እና የማንቸስተር ሲቲውን ሮድሪን የውድድሩ ኮከብ ተጫዋቾች አድርጎ አስመርጧል።

በወጣት ቡድኖች ጀምሮ ታሪክን የሰራው አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፎንቴም ዛሬ የቪሰንቴ ዴልቮስኬን ታሪክ በመጋራት የሀገሩ ኩራት መሆን ችሏል።

ስፔንን ከወጣት ጀምሮ በተለያዩ የዕድሜ እርከኖች ብሔራዊ ቡድኖቿን ያሰለጠኑት አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፎንቴ፤ በአንድ ወቅት ስራ አጥተው የማስታወቂያ ሰሌዳዎችን ለማንበብ እንዳልኳተኑ አሁን ትልቁን ዋንጫ አንስተዋል፤ የቆፍጣናውን አሰልጣኝ ቪሰንቴ ዴልቮስኬንም ታሪክ ተጋርተዋል። “እነርሱ ለስፔናውያን ኩራት የሆኑ ድንቅ የእግር ኳስ ትውልዶች ናቸው፤ በማበራችን ጠንክረናል፣ አሸንፈናልም” የሚለው የሉዊስ ዴ ላ ፎንቴ ሃሳብ ነው።

ላ ሮሃ የዓለም ሻምፒዮን!

በእድሪስ አህመድ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: