Search

ተፈጥሮን የመካስ ሀገራዊ ጉዞ ፤ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር

ማክሰኞ ሐምሌ 14, 2018 74

በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ምድሯን በለምለም ካባ ያለበሰችው ኢትዮጵያ፤ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከልና ተፈጥሮን በመጠበቅ   አስደማሚ ታሪክ በመጻፍ ላይ ትገኛለች።

ባለፉት 8 ዓመታት  በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር  አማካኝነት 48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች  መተከል ተችሏል።

ሚሊዮኖች እየተሳተፉበት በቀጠለው መርሐ ግብር በቀጣይ ዓመታት 65 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል እየተሰራ ነው።

 እስካሁን በተሰሩ ሥራዎች  በድርቅና በአፈር መሸርሸር የተራቆተ መሬት፣ ተራራዎች  እና  የወንዝ ዳርቻዎች መልሰው  እንዲያገግሙ ማድረግ ተችሏል።

ይህ ታላቅ ጥረት የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ስነምህዳር ከማደስ ባለፈ ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃ እና በአረንጓዴ ዲፕሎማሲ አርኣያ ሆና እንድትወጣ አስችሏታል።

ይህ የአረንጓዴ ንቅናቄ የኢትዮጵያን ዋና ዋና ከተሞችና የቱሪስት መዳረሻዎች ገፅታ በመቀየር ረገድም  እጅግ ከፍተኛ ድርሻ አበርክቷል።

በተለይም ከኮሪደር ልማትና ከፓርኮች ግንባታ ጋር እየተካሄደ ያለው የአረንጓዴ ልማት ስራ ለዜጎች ምቹና ጽዱ የኑሮ አካባቢን ከመፍጠሩም በላይ የከተማ ቱሪዝምን አነቃቅቶታል።

ከዚሁ ጎን ለጎን የተተከሉት የፍራፍሬና የተለያየ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያላቸው ዛፎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ለዜጎች ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለመፍጠር አዲስ ተስፋ ፈንጥቀዋል።

የአረንጓዴ ሻራ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ለተፈጥሮ የምትሰጠውን ትልቅ ግምትና የነገውን ትውልድ ተስፋ የማስጠበቅ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ምስክር ነው።

የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብና በማሳደግ በኩል እየተደረገ ያለው የጋራ ርብርብ ሀገራችን የተፈጥሮ ሚዛኗ የተጠበቀ አረንጓዴና ውብ እንድትሆን አስችሏል።

 የኢትዮጵያ  ሁለንተናዊ የልማትና የተፈጥሮ እንክብካቤ ጉዞ ለመላው አፍሪካ ተስፋ በመሆን የይቻላል ትዕምርት ሆኖ ቀጥሏል።

በሃና ምንዳሁን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: