Search

የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገትን ለማፋጠን የተፈጥሮ ሀብትና የዱር እንስሳት ጥበቃ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ

ማክሰኞ ሐምሌ 14, 2018 78

የተፈጥሮ ሀብትና የዱር እንስሳት ጥበቃ ሥራዎች ለቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት ያላቸውን አስተዋጽኦ ይበልጥ የሚያጎሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (/) ገለጹ።

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን 60 ዓመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ መርሃ ግብሮች እያከበረ ይገኛል።

በመድረኩ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (/) በመድረኩ ባደረጉት ንግግር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ሀሳብ አመንጪነት እውን የተደረጉት የገበታ ለሀገር፣ የገበታ ለሸገር እና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ለቱሪዝም ዘርፉ አዲስ ምዕራፍ የከፈቱ መሆናቸውን አንስተዋል።

ባለፉት ዓመታት ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ በተሰጠው ልዩ ትኩረትም የዱር እንስሳት ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ መደረጉን አስረድተዋል።

በተጨማሪም በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት እየተተገበረ ያለው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብር አሁን ያለው ትውልድ የተፈጥሮ ሀብትን በመንከባከብ ረገድ ያለውን አደራ በብቃት እንዲወጣ እንዳስቻለው ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በበርካታ ብርቅዬ የዱር እንስሳት በልዩ ልዩ የተፈጥሮ ሀብቶች እና በውብ ሥነምህዳሮች የታደለች ሀገር መሆኗን ጠቅሰው እነዚህን የተፈጥሮ ጸጋዎች ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የሁሉም የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ ለተፈጥሮ ሀብት እና ለዱር እንስሳት ጥበቃ በሰጠችው ከፍተኛ ትኩረት የኢትዮጵያን የደን ሽፋን ማሳደግ መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡

የቱሪዝም እድገት ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ በመሆኑ፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተፈጥሮ ሀብትና የዱር እንስሳት ጥበቃ ሥራዎችን አጠናክሮ ለመቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ የዱር እንስሳት ጥበቃው ጉዞ በብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ ያለፈ መሆኑን በማስታወስም ለዘርፉ ዕድገትና ለዱር እንስሳት ጥበቃ ሥራዎች አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ሁሉ ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: