Search

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዕለታዊ መግለጫ ላይ የተነሱ ዋና ዋና ሐሳቦች፦

ሓሙስ ሐምሌ 16, 2018 77

የውይይቱ ሒደት እና ተሳትፎ፦ 4 ሺህ ተሳታፊዎች በንዑሳን ቡድኖች (10 እስከ 50 አባላት) ተከፋፍለው ከፍተኛ መተማመን በታከለበት ሁኔታ በነፃነት እየተወያዩ ነው። በቀጣይም እነዚህ ቡድኖች ወደ 250 አባላት ስብስብ ከፍ ብለው ውይይታቸውን ይቀጥላሉ።

ሙሉ የደኅንነት ዋስትና እና ከለላ፦ ተሳታፊዎች ያለምንም ፍርሃት እና ገደብ ሐሳባቸውን እንዲገልጹ መደረጉ እና በመድረኩ ለሚያነሡት ማንኛውም ሐሳብ ኮሚሽኑ ሙሉ ኃላፊነት እና ከለላ የሚሰጥ ሲሆን በየትኛውም የውጭ አካል ተጠያቂ እንደማይሆኑ ዋስትና ተሰጥቷቸዋል።

የምሁራን ተሳትፎ፦ በሀገረ መንግሥት ግንባታ፣ በታሪክ፣ በማንነት፣ በፌዴራሊዝም እና በግጭት አፈታት ዙሪያ ጥልቅ ዕውቀት ባላቸው ምሁራን ገለጻ እየተደረገ ሲሆን፣ 8 ማዕከላት ከተከፈሉት ተሳታፊዎች ጋርም ሰፊ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

ጥንቃቄ ከሐሰተኛ መረጃዎች፦ የውይይቱ የመጀመሪያ ደረጃዎች ስሜት የተሞላባቸው ሊሆኑ ስለሚችሉ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ለሚሠራጩ ያልተጣሩ መረጃዎች ኅብረተሰቡ እና ሚዲያዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገልጿል።

ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ፦ የተሳሳቱ መረጃዎችን ለመከላከል ይፋዊ እና ዕለታዊ መረጃዎች የሚሰጡት በዋና ኮሚሽነሩ፣ በምክትል ዋና ኮሚሽነሯ ወይም በሚዲያ አስተባባሪ ኮሚሽነሮች አማካኝነት ብቻ ነው።

ልዩ እና አስደሳች አጋጣሚ፦ በምክክሩ ሒደት ላይ ከቤኒሻንጉል የመጣች አንዲት ተሳታፊ እናት "ኮሚሽን" የሚል ስም የወጣለት ሕፃን ልጅ በሰላም መውለዷ መድረኩ ላይ ልዩ ድባብ ፈጥሯል! ከባድ ሕክምና የተደረገላቸው ሌሎች ተሳታፊዎችም አገግመው ወደ መድረኩ ተመልሰዋል።

በለሚ ታደሰ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: