Search

አቅመ ቢሶቹ የሞት ነጋዴዎች

ሓሙስ ሐምሌ 16, 2018 89

ሕገ ወጡ የሕወሓት ቡድን ትናንትም ሆነ ዛሬ ከተላላኪነት እና ከተራ አፍራሽነት ያላለፈ ምንም ዓይነት አቅም የሌለው ስብስብ ነው።

የአንድ ሀገር ጥንካሬ በሚለካባቸው ተቋማት ላይ ጥፋት ሲፈፅም የኖረው ይህ ራዕይ የሌለው ቡድን አሁንም ከተራ ሌብነቱ ሊያድግ አልቻለም።

ከምሥረታው ጀምሮ ከጥፋት በቀር በጎ ታሪክ የሌለው ይህ ደካማ ስብስብ፣ ለብዙዎች መከራ ምክንያት ከመሆን ያለፈ ፋይዳ የለውም።

የትግራይ ሕዝብ "ፍላጎታችን ሰላም እና ልማት ነው" እያለ፣ ተላላኪው ቡድን ግን የሚያውቀው የተለመደችውን የሽፍትነት ተግባር ስለሆነ የሀገር ሀብት የሆነውን የወርቅ ማዕድን በኮንትሮባንድ ሽጦ ክላሺንኮቭ ይሸምታል።

ወርቅን ሸጦ የጦር መሣሪያ የሚገዛው ይህ አቅመ ቢስ ቡድን ዛሬም ራሱን ማዳን አቅቶት የትግራይን ወጣት ለከንቱ ውድመት ይማግዳል።

ማዕድን የሀገር ሀብት ቢሆንም በዚህ ተራ ዘራፊ ቡድን እጅ ሲወድቅ ግን የደም ዋጋ መሆኑ አልቀረም።

የትግራይ ሕዝብ ጦርነት እንደማይፈልግ በአደባባይ ጭምር በግልጽ እያሳየ፣ ወላጆች ልጆቻቸው ተምረው እና ትዳር መሥርተው እንዲያዩ እየተመኙ፣ ይህ ፖለቲካዊ ኪሳራ የገጠው ሐሳብ አልቦ ስብስብ ግን ወጣቱን እንደ ርካሽ የጦርነት ማገዶ ከመቁጠር አልተቆጠበም።

ትግራይ የሚያስፈልጋት ሰላም እንጂ ከዚህ ደካማ ቡድን የሚመጣ መሣሪያ አይደለም። ማዕድናት እና የተፈጥሮ ሀብትም ቢሆን ለትግራይ ሕዝብ ዕድገት እና ለወጣቶች ሥራ መፍጠሪያ መሆን ሲገባው ለዚህ ራዕይ አልባ ቡድን የተራ መሣሪያ መግዣ ሆኗል።

ሕዝቡም ይህንን አቅም ያጣ የሞት ነጋዴ "በቃህ" ብሎ አሽቀንጥሮ ሊጥለው ይገባል፤ የወጣቶች ሕይወት የዚህ ተራ ስብስብ የሥልጣን ጥም ማርኪያ መሆኑ ሊያበቃ ግድም ይላል።

ይህ የማፊያ ስብስብ ለዓመታት ከሌብነት የዘለለ ዓላማ ያልነበረው ሲሆን ያካበተውን ይህን ሕገ ወጥነት ይዞ ወደለመደው ተራ ሽፍትነት በመውረድ፣ በሕገ ወጥ ሰዎች ዝውውር እና የሽብር ተግባራት ውስጥ ተዘፍቋል።

ይህ ቡድን አቅመ ቢስነቱን ለመሸፈን እንደለመደው የታሪካዊ ጠላቶች ጫማ ሥር ወድቆ በመላላክ የውርደት ካባውን ደርቧም።

የቡድኑ አካሄድ ከፋሺስትም ሆነ ከሌሎች ጠላቶች የሚለየው ታላቅ አቅም ኖሮት ሳይሆን ታሪክ የማይረሳው የውስጥ ባንዳ እና ተራ ዘራፊ በመሆኑ ብቻ ነው።

በትልቅ የገዢ ወንበር ላይ ተቀምጠው እንኳ ከመዝረፍ በቀር ምንም መማር ያልቻሉት እነዚህ ግለሰቦች፣ ዛሬም ያቺው የዝርፊያ መንገዳቸው እንዳትዘጋባቸውና ሕልውናቸውን ለማቆየት ሕዝቡን ለማወናበድ ይሞክራሉ።

ኢትዮጵያን እና ፖለቲካዋን ለማበላሸት ሲቋምጥ የኖረው ይህ ስብስብ፣ በመጨረሻም የገዛ ራሱን ጉድጓድ ከመቆፈር የዘለለ ያመጣው ትልቅ ስኬት የለም። ዛሬም እንደ ትናንቱ በባንዳነት ከውጭ ጠላቶች ጋር ለመሰለፍ ቢሞክርም፣ የዚህ ተራ ስብስብ ጀምበር ከጠለቀች ውሎ አድሯል።

ምንም አቅም የሌላቸው እነዚህ ኮንትሮባንዲስቶች ከዛሬዋ ግዙፍና ጠንካራ ኢትዮጵያ ጋር መጋጨት ቀርቶ ማሰብም አይችሉም። ሀገርን ለመታደግ ከሚተጋው ኃያል ኃይል ጋር ለመጋጨት ቢሞክሩም ትርፋቸው እንደለመዱት መፈረካከስና የባሰ መላላጥ ብቻ ይሆናል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: