Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ለታቀደው ሀገራዊ መርሐ-ግብር ዜጎች ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ

ረቡዕ ሐምሌ 22, 2018 133

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ ለመሥራት ለታቀደው ሀገራዊ መርሐ-ግብር አምስት ቀናት ብቻ መቅረታቸውን በመጠቆም፣ መላው ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢትዮጵያውያን ክንድ ተባብሮ በአንድነት ለሚመዘገበው ታሪካዊ ድል እውን መሆን ዜጎች በቁርጠኝነት ሊነሡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

"በጋራ ተስፋን እንትከል!" በማለት ውድ ኢትዮጵያ ልጆች በቀሪዎቹ ቀናት ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው በዕለቱ በንቃት እንዲሳተፉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: