Search

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ያቀድነውን ሁሉ አሳክተናል

ሓሙስ ሐምሌ 23, 2018 91

በኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ከተጀመረበት የ2011 ጀምሮ እስከአለፈው ክረምት 2018 በየዓመቱ የታቀዱ እና በተግባር የተተከሉ የችግኝ መጠኖች የዛሬ ብርታትም ጭምር ናቸው።

በሁሉም ዓመታት የተተከለው የችግኝ መጠን ከታቀደው በላይ ወይም ሙሉ በሙሉ ዕቅዱን ያሳካ ሆኖ ተመዝግቧል።

በዚህም መሠረት በ2011 ታቅዶ ከነበረው 4 ቢሊየን በላይ 4.7 ቢሊየን፣ በ2012 ከ5 ቢሊየን ዕቅድ 5.9 ቢሊየን፣ በ2013 ከ6 ቢሊየን ዕቅድ 6.8 ቢሊየን፣ በ2014 ከ6 ቢሊየን ዕቅድ 7.2 ቢሊየን፣ በ2015 ከ6.5 ቢሊየን ዕቅድ 7.5 ቢሊየን፣ በ2016 ከ6.5 ቢሊየን ዕቅድ 7.6 ቢሊየን እንዲሁም በ2017 የታቀደው 7.5 ቢሊየን ችግኝ ሙሉ በሙሉ ተተክሏል።

ይህ በየዓመቱ እያደገ የመጣው አበረታች ስኬት፣ የሕዝባችንን አረንጓዴ አሻራ የማሳረፍ ቁርጠኝነት እና ለነገዋ የበለጸገችና ለምለም ኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን ታላቅ ጥረት በግልጽ ያሳያል።

በዚህ አመትም ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እየተሳተፉ አሻራዎን እያስቀመጡ ነው?

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: