የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከካሜሮን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌዡን ምቤላ ምቤላ ጋር በሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸው ወቅት ሚኒስትሮቹ ኢትዮጵያና ካሜሮን ጠንካራና ታሪካዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ሁለቱ ሀገራት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን 60ኛ ዓመት ለማክበር በዋዜማ ላይ በሚገኙበት በዚህ ወቅት፣ ከፖለቲካዊ ዲፕሎማሲ ባሻገር በኢኮኖሚው ዘርፍ ጠንካራ ትስስር መፍጠር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
በሌላ በኩል የካሜሮን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌዡን ምቤላ ምቤላ ኢትዮጵያ 49ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ በስኬት በማጠናቀቋ የተሰማቸውን አድናቆት ገልጸዋል።
አክለውም ኢትዮጵያ ኅብረቱን በፋይናንስ አቅም ለማጠናከር ያሳየችውን ቁርጠኝነትና ያሳለፈችውን ውሳኔ በማድነቅ የሀገራቸውን ሙሉ ድጋፍ ማረጋገጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: