Search

ከ200 ሚሊዮን እስከ 800 ሚሊዮን የኢትዮጵያ የማይበገር የተስፋ ጉዞ

ዓርብ ሐምሌ 24, 2018 112

ኢትዮጵያ 2011 . በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) አነሳሽነት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን ብላ ስትጀምር ዓላማዋ አካባቢን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ታሪክ እና የዜጎችን አስተሳሰብ የመለወጥ ትልቅ ራዕይ ነበረው።

2011 . በየዓመቱ ከሚተከለው በርካታ ቢሊዮን ችግኞች በተጨማሪ "በአንድ ሰው 40 ችግኝ" እንዲሁም "በአንድ ጀምበር 200 ሚሊዮን ችግኝ" ለመትከል እቅድ ተይዞ ወደ ተግባር ሲገባ በርካቶች "ይህ አይሆንም፣ ቅዥት ነው" በማለት ተስፋ ለማስቆረጥ ጥረት አድርገው ነበር።

ሆኖም ኢትዮጵያውያን በነቃ ሕዝባዊ ንቅናቄ እና በተግባር በሰጡት ምላሽ በአንድ ጀምበር ዘመቻ ታቅዶ የነበረውን 200 ሚሊዮን አልፎ ሐምሌ 22 ቀን 2011 . በመላ ኢትዮጵያ 353 ሚሊዮን 633 ሺህ 660 ችግኞችን መትከል ተችሏል፡፡

2011 እስከ 2018 . የተመዘገበው የጽናት እና የተስፋ ጉዞ ከስድስት ዓመታት በፊት የተዘራው የችግኝ ተከላ ዘመቻ ዛሬ ላይ ከዘመቻ ሥራ ወጥቶ የመላው ኢትዮጵያዊ ባህል እና መለያ መሆን ችሏል።

አይሆንም ላሉት አካላት በየዓመቱ በሥራ እና በውጤት እየመለሰች የመጣችው ኢትዮጵያ፣ 2018 . "ተስፋን እንትከል " በሚል ታላቅ ሀገራዊ መሪ ቃል ሂደቱን በይፋ ጀምራለች።

ይህ 2011 . በአንድ ጀምበር 200 ሚሊዮን ዕቅድ የተነሳው ንቅናቄ ዛሬ በአንድ ጀምበር ወደ 800 ሚሊዮን ማደጉ በሀገራችን በየዓመቱ እያደገ የመጣውን አቅም በግልጽ ያሳያል።

2011 . ጅማሮ ትልቁ ስኬት "አይቻልም" የሚለውን የጠላት እና የተስፋ አስቆራጮችን ትርክት በመስበር በኅብረት ከተነሳን ማሳካት እንችላለን የሚል ፅኑ ሀገራዊ እምነት መፍጠሩ ነው።

2011 . የተጀመረው ሥራ አፈር ከመሸርሸር እና ከደን ጭፍጨፋ መከላከል ቢሆንም 2018 . ግን እንደ ማካዴሚያ፣ ኮኮናት፣ ቡና እና የፍራፍሬ ተክሎችን በስፋት በማካተት የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሬ ገቢ የሚያሳድግ እና የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ ዘመናዊ የልማት ምሰሶ ሆኗል።

"ተስፋን እንትከል" የሚለው የዘንድሮው መሪ ቃል በፈተናዎች ውስጥ ያለችውን ሀገር በኅብረት እና በአረንጓዴ ልማት እርስ በእርስ በማስተሳሰር ለቀጣዩ ትውልድ የተረጋጋች እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ያለውን ጽኑ ፍላጎት ያመላክታል።

2011 . 353 ሚሊዮን በላይ የአንድ ጀምበር ተከላ የተጀመረው የተስፋ ጉዞ ዛሬ 2018 . 800 ሚሊዮን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ሊጽፍ ዝግጅቱን ጨርሷል።

ኢትዮጵያ ለሚነሱባት ጥርጣሬዎች በተግባር እየመለሰች የተተከሉ ችግኞች አድገው ፍሬ ማፍራት እንደጀመሩት ሁሉ የዕድገት እና የሰላሟ ተስፋም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ይሄዳል።

በሃና ምንዳሁን

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: