Search

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ከጎንደር ሁመራ ቋሚ የበረራ አገልግሎት ሊጀምር ነው

ዓርብ ሐምሌ 24, 2018 110

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሐምሌ 25 ቀን 2018 . ጀምሮ ከጎንደር ወደ ሁመራ የበረራ አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

የበረራ አገልግሎቱ ዘወትር ቅዳሜ ከጎንደር ወደ ሁመራ የሚደረግ ሲኾን ዘወትር ሰኞ ደግሞ ከሁመራ ወደ ጎንደር አገልግሎት እንደሚሰጥ ነው ያስታወቀው።

አየር መንገዱ የሀገር ውስጥ በረራ መዳረሻዎችን በማስፋት ሕዝብን ለማገልገል እንደሚሠራ የገለጸ ሲኾን ከጎንደር ሁመራ የተጀመረው አገልግሎትም ማኅበራዊ ግንኙነትን ከፍ የሚያደርግ ይሆናል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: