Search

የአማራ ክልል የ2019 ዓመታዊ በጀት ከ402 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኖ ጸደቀ

ቅዳሜ ሐምሌ 25, 2018 98

የአማራ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 6 ዙር 5 ዓመት የሥራ ዘመን 12 መደበኛ ጉባኤ 2019 በጀት ዓመት ለክልሉ የልማት ሥራዎች ማስፈጸሚያ በጀት 402 ቢሊዮን 285 ሚሊዮን 713 ሺህ 544 ብር ሆኖ አጽድቋል።

2019 በጀት ዓመት አጠቃላይ በጀቱ 2018 በጀት ዓመት ከተመደበው 78 ነጥብ 4 በመቶ ወይም 176 ቢሊዮን 831 ሚሊዮን 934 ሺህ 307 ብር ዕድገት እንዳለው የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኀላፊ አታላይ ጥላሁን ገልጸዋል፡፡

ከዓመታዊ በጀቱ 71 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆነው በክልሉ ከሚሠበሠብ ገቢ፣ 27 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆነው ከፌዴራል መንግሥት ጥቅል የቀመር መደበኛ ድጋፍ ድርሻ እንዲሁም ቀሪው ደግሞ ከልዩ ልዩ ምንጮች እንደሚሸፈን ተገልጿል።

የተመደበው በጀት በዓመቱ ለዘላቂ ልማት ዕቅድ ማስፈጸሚያ፣ ለልዩ ልዩ ሪፎርሞች እና መዋቅራዊ ማሻሻያዎች፣ ለድህነት ተኮር ሥራዎች እና የክልሉን የመልማት አቅም ታሳቢ ያደረገ ስለመሆኑም ተመላክቷል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ 2018 በጀት ዓመት የክልሉ መንግሥት ሥራ ላይ ላዋለው 39 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ የተጨማሪ በጀት አጽድቋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: