Search

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባሕል ግንባታ ከትናንት እስከ ዛሬ

ቅዳሜ ሐምሌ 25, 2018 131

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ታሪክ እጅግ ረጅም፣ ውጣ ውረድ የበዛበት እና የገዛ ልጆቿን ደም ሲጠጣ የኖረ ፈታኝ ጉዞ ነው። የፖለቲካ ባሕላችንን ከትናንት ማለዳ አንስቶ እስከ ዛሬው ዘመን ስንቃኝ፣ ከፍጹም መለኮታዊ እና አፋኝ አገዛዝ አንስቶ እስከ ደም አፋሳሽ አብዮቶች፣ ከውጭ የተቀዱ ርዕዮተ ዓለሞች ፍጭት እስከ አምባገነንነት እንዲሁም ከጥላቻ ፖለቲካ እስከ ዛሬው የሠለጠነ የምክክር አውድማ ድረስ የተጓዝንበትን አስገራሚና ስብራት የበዛበትን መንገድ እንመለከታለን።

19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ አንስቶ እስከ 1950ዎቹ ድረስ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባሕል መሠረቱ ሃይማኖታዊ እና መለኮታዊ ነበር። በክብረ ነገሥት ትርክት ላይ የተንጠለጠለው የሥልጣን ምንጭ፣ንጉሥ አይከሰስ፣ ሰማይ አይታረስበሚል ብሂል የሕዝብን ፍጹም ተገዢነት ያረጋገጠ ነበር። ሥልጣን የሚገኘውም ሆነ የሚጠበቀው በመለኮታዊ ቅቡልነት እንጂ በሕዝብ ይሁንታ አልነበረም፤ የዜጎች ተሳትፎም በማጎብደድ የታጠረ ነበር።

1950ዎቹ ወዲህ የዘመናዊ ትምህርት መስፋፋትን ተከትሎ ይህ የረጋ የፖለቲካ ባሕል መንቀጥቀጥ ጀመረ። የተማረው የኅብረተሰብ ክፍል የነገሥታቱን መለኮታዊ ቅቡልነት በይፋ ሞገተ። ነገር ግን፣ 1960ዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ የውጭ ርዕዮተ ዓለሞችን (ሶሻሊዝምና ኮሚኒዝምን) ከሀገር ነባራዊ እውነታ ጋር ሳያጣጥሙ እንደወረዱ ለመተግበር መሞከሩ፣ የፖለቲካ ሜዳውን የልፍለፋ፣ የፉክክር እና የጽንፈኝነት መድረክ አደረገው። ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህንአፋዊ ሆንን... ቤታችንስ አንድ ነው!” በማለት የገለጸው ይህንን የትውልዱን ሥነ ልቦናዊ ስብራት እና ሚዛን ማጣት ነበር።

በተለይም የተጎዳው እና የፖለቲካ ባሕላችን ክፉኛ የጨነገፈው አብዮቱን ተከትሎ በመጣው የደርግ ዘመን ነው። አብዮቱን ተከትሎ የተለያዩ የፖለቲካ ቡድኖች ቢፈጠሩም፣ ሐሳብን በጠረጴዛ ዙሪያ አቅርበው የፖለቲካ ባሕሉን ወደ ሠለጠነ ውይይት ለማምጣት የነበራቸው ዕድል ሙሉ ለሙሉ ጨነገፈ። የሕዝቡን ጩኸት ተጠቅሞ ሥልጣን የያዘው ደርግ እና በተቃራኒው የተሰለፉ ኃይሎች፣  በመመካከርና በመነጋገር አብሮ ለመሥራት የነበሩ እድሎችን በአጉል ግትርነትና እኔ አውቅልሀለው ብሂል አደፈረሱት፡፡ አንድ ትውልድ "ቀይ ሽብር" እና "ነጭ ሽብርየደም መንገድ አለቀ። በሀገራችን "ፖለቲካና ኮረንቲ በሩቁ" የሚል የከፍተኛ ድባቴ እና የፍርሃት ዘመን ተፈጠረ።

ደርግ አብዛኛውን ዘመን ያሳለፈው ችግሮችን ሁሉ በጠብመንጃ አፈሙዝ የመፍታት አባዜ ውስጥ ተዘፍቆ ነበር። በምሥራቁ የሀገራችን ክፍል ያገኘነውን ድል፣ "በሰሜንም አለን" ብሎ በማወጅ የገዛ ዜጎቹን በጦርነት አስፈጀ። ይህ አካሄድ መፍትሔ አልባ እና ፍትሐዊ ያልሆነ ደም መፋሰስን አስከተለ። በዚህ ዘመን የፖለቲካ ባሕላችን "ጠብመንጃ እና ጠብመንጃ ብቻ" "ጉልበት እና ጉልበት" "አሸናፊ እና ተሸናፊ" እንዲሁም "ጠላት እና ወዳጅ" የሚል ጽንፈኛ መልክ ያዘ። መነጋገር የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሶ፣ የፖለቲካ ጉዟችን ፍጹም ወደሆነ ቁልቁለት አዘቀዘቀ።

1983 . ኢሕአዴግ ሥልጣን ሲይዝ፣ መጀመሪያ ላይ የሐሳብ ገበታን የሚያሰፋ መስሎ ነበር። በሽግግር መንግሥቱ ምስረታ ጅማሮ ላይ፣ ከደርግ ኢሠፓ ውጪ የሆኑ በርካታ የፖለቲካ ኃይሎች በሒደቱ እንዲሳተፉ መደረጋቸው ተስፋ ሰጪ ነበር። ነገር ግን፣ ይህ ጅማሮ በአጭሩ ተቀጨ። ኢሕአዴግ ለይስሙላ የከፈተውን የሽግግር ሒደት ቀስ በቀስ በማጥበብ፣ እያንዳንዱን ኃይል እየገፋ በማስወጣት ሜዳውን ብቻውን ተቆጣጠረው። 1987 ሕገ መንግሥት ወዲህ ደግሞ ሥርዓቱ ወደ ፍጹም አምባገነንነት ተቀየረ። በምርጫ ስም ስፍር ቁጥር የሌለው ፖለቲካዊ ደባ ተፈጸመ።

የፖለቲካ ባሕሉ እርስ በርስ መነጋገርን እንደ መጥፎ ድርጊት ወደሚቆጥርበት ደረጃ ወረደ።እኔ አውቅልሃለሁየሚለው ፖለቲካ ገኖ ወጣ። "እኔ አውቃለሁ አንተ አታውቅም" "እኔ እችላለሁ አንተ አትችልም" "አንተ ጠላት ነህ እኔ ደግሞ ወዳጅ ነኝ" የሚለው እብሪት ጠረጴዛን የሚያገል እና መነጋገርን የማይፈቅድ አፋኝ ሥርዓት ፈጠረ። 1997 . ምርጫ ወቅት የፖለቲካ ባሕሉ በተወሰነ ደረጃ የመሻሻል ምልክት ቢያሳይም፣ መልሶ ግን ሒደቱን ገዥው መንግሥት በገዛ እጁ አበላሸው። የፖለቲካ ባሕላችን ጊዜ በጊዜ፣ ሒደት በሒደት፣ ይበልጥ ከዘመን ዘመን አጣብቂኝ ውስጥ እየገባ፣ ለመጠገን ሥር ነቀል ለውጥ የሚፈልግ ጥልቅ ስብራት ሆነ።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ ሀገራዊ ለውጡ እውን ከሆነ በኋላ ግን፣ ይህ የፖለቲካ አካሄድ ቀና ማለት ጀመረ። የፖለቲካ ባሕላችን እንዲሻሻል በለውጡ ማግስት በርካታ እርምጃዎች ተወስደዋል። በተከፈተው የፖለቲካ በር (Political open-up) በርካታ የተገፉ ኃይሎች ወደ ሀገር ገቡ። ዜጎች ሐሳባቸውን በነፃነት ማንጸባረቅ ጀመሩ፣ የተለያዩ የተዘጉ ሚዲያዎች ተከፈቱ፣ እስረኞችም ተለቀቁ። ይህ ለፖለቲካ ባሕሉ መሻሻል እጅግ ትልቅ እርምጃ ነበር።

ይሁን እንጂ፣ ይህ ብቻውን በቂ አልነበረም፤ ባሕል በአንድ ጀምበር አይሰፍንምና። የኖርንበት እና የዳበረው የተበላሸ የፖለቲካ ባሕል በአንድ ጊዜ ለመጠገን እጅግ ፈታኝ ነው። ይህ የፖለቲካ ባሕል በማኅበረሰቡ ውስጥ በጥልቀት የሰረጸ ከመሆኑም በላይ፣ አሁን ያሉት የፖለቲከኞች ስብስብ የተቀዳው ከዚሁ ካለፈው የፖለቲካ ሥርዓት በመሆኑ፣ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የተወሰነ ጊዜ የሚፈጅ መሆኑ እሙን ነው።

ነገር ግን፣ በጣም መሠረታዊ የሆኑ እርምጃዎች ተወስደዋል። የምርጫ ሒደቱ እየተሻሻለ፣ የፖለቲከኞች አብሮ ተባብሮ የመሥራት ዕድል እየሰፋ መጥቷል። ባለፉት አምስት ዓመታት፣ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች ከመንግሥት ጋር አብረው የሚሠሩበት፣ መንግሥትን በነፃነት እየተቹም ቢሆን ሀገርን በጋራ የሚያገለግሉበት አዲስ ባሕል ተፈጥሯል።

ከዚህ ሁሉ በኋላ ደግሞ፣ ሀገራዊ ምክክሩ እውን መሆን እጅግ አስደናቂ የሆነ የፖለቲካ ባሕል ግንባታ ደረጃ ለመፍጠር የሚያስችል ፍጹም የተለየ ምዕራፍ ነው። ይህን ቁርጠኝነት መንግሥት በተግባር ማሳየቱ፣ ሀገራችን ለዘመናት ከተዘፈቀችበት የጥላቻ ማጥ እንድትወጣ ትልቅ በር ከፍቷል። አሁን ላይ፣ የተለያየ እና ተቃራኒ አቋም ያላቸው ሰዎች አንገት ለአንገት ከመተናነቅ ይልቅ፣ ጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብለው መነጋገር መጀመራቸው በኢትዮጵያ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ነው።

ይህ የምክክር መድረክ፣ ኢትዮጵያ አዲስ የፖለቲካ ባሕል ግንባታ መስመር ውስጥ መግባቷን በጉልህ ያሳያል። ዜጎች ለመደማመጥ ፈቃደኛ መሆናቸው፣ ከመገዳደል እና ጠብመንጃን ከማስቀመጥ ባሻገር በጠረጴዛ ዙሪያ መገኘታቸው ታላቅ ድል መሆኑን የሚያበስር ነው። ይህ ቆም ብሎ መነጋገር፣ የተበላሸውን ትናንት አርሞ በጋራ መጻኢ ዕድል ላይ መምከር፣ እያደገ ለሚሄደው ጠንካራ የሀገረ መንግሥት ግንባታ (State-building) ታላቅ ዕድል መሆኑን የሚያረጋግጥ የማይናወጥ የሰላም ምሰሶ ነው!

 በአዶኒያስ ወልደአረጋይ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: