Search

የተዛቡ የፖለቲካ አሠራሮችን በማረም አካታች እና ዴሞክራሲያዊ የመንግሥት ሥርዓት ተገንብቷል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ቅዳሜ ሐምሌ 25, 2018 61

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ዓመታት የነበሩ የተዛቡ የፖለቲካ ውክልናዎችን በማስተካከል የሁሉንም ብሔሮች እና ክልሎች እኩል ተሳትፎ ማረጋገጥ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ከለውጡ በፊት በገዢው ፓርቲ ውስጥ የነበረው አሠራር ዴሞክራሲያዊነትን የተከተለ እንዳልነበር ጠቅሰው፣ በዚህም ምክንያት አነስተኛ አባላት ያሉት ፓርቲ ከትልቁ ጋር እኩል ድምጽ ኖሮት አብላጫውን ሕዝብ የሚገዛበት አግባብ እንደነበር አስታውሰዋል።

ይሁን እንጂ የብልጽግና ፓርቲ ይህን ብልሹ አሠራር በማረም እና የክልሎችን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በማረጋገጥ በኩል ወሳኝ እርምጃ መውሰዱን አብራርተዋል።

በተጨማሪም በሀገራችን ቁልፍ የኢኮኖሚ እና የጸጥታ ተቋማት ውስጥ ይታይ የነበረውን የአካታችነት ችግር በመፍታት ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖር መደረጉን አንስተዋል።

መንግሥት አንዱን እንደ ገዢ ሌላውን እንደ ጨቋኝ የሚፈርጁ አጥፊ ትርክቶችንም እያረመ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በካቢኔ እንዲሁም በፓርላማ በማሳተፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አካታች የፖለቲካ ሥርዓት መገንባቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

በለሚ ታደሰ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: