Search

በጋምቤላ ክልል የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃግብር ለማከናወን ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቋል

እሑድ ሐምሌ 26, 2018 70

በጋምቤላ ክልል በነገው ዕለት የሚካሄደውን የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ስራ በማህበረሰቡ ተሳትፎ ለማሳካት ቅድመ ዝግጅቱ መጠናቀቁ ተገልጿል።

የአረንጓዴ አሻራ ስኬቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል እንደ ሀገር ሀምሌ 27/2018 . በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል የተያዘውን ግብ መሰረት በማድረግ በክልሉ የተከላ ቦታዎችን የመለየት የችግኝ ጉድጓድ የማዘጋጀትና ችግኞችን ወደ ተከላ ቦታ የማድረስ ተግባር ተከናውኗል።

በክልሉ በረሃማነትን ለመከላከልና የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚያስችል ቀጣይነት ያለው የአካባቢ ጥበቃ ስራና የችግኝ ተከላ እየተከናወነ ሲገኝ በዚህም የተራቆቱ ስፍራዎች መልሰው በማገገማቸው የደን ሽፋንም እየጨመረ መጥቷል።

በዕለቱ የችግኝ ተከላው በሚከናወንባቸው 17 የተከላ ቦታዎች ላይ የተለያዩ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸውን የደንና የፍራፍሬ ችግኞችን በአግባቡ ለመትከል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል።

ማህበረሰቡ እንደ ቀደመው ጊዜያት በነቂስ ወጥቶ ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ ለአረንጓዴ አሻራ ስኬት የሚያደርገውን ተሳትፎ ሊያጠናክር እንደሚገባም ተመላክቷል።

በሚፍታህ አብዱልቃድር

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: