Search

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ዝግጅት ተጠናቀቀ

እሑድ ሐምሌ 26, 2018 74

በመላው ሀገራችን በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል በተያዘው ታላቅ ሀገራዊ መርሐ ግብር መሠረት፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልም ለተከላው የሚጠየቀው ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል።

ሐምሌ 27 ቀን 2018 . በሚካሄደው በዚህ ታሪካዊ የአረንጓዴ ዐሻራ ዘመቻ 16 ሺህ 516 ሄክታር በላይ መሬት በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በተለያዩ አርሶ አደሮች ማሳ ላይ የሚተከሉ ችግኞችም በዕለቱ መርሐ ግብር ውስጥ ተካትተዋል።

መርሐ ግብሩ ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥን እና የአርሶ አደሩን ገቢ ማሳደግን ዓላማ ያደረገ ነው።

በመሆኑም አቮካዶ፣ ፓፓያ፣ ማንጎ፣ አፕል፣ ቡና እና ሌሎች የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ እንደ እንሰት ያሉ ዝርያዎች ለዕለቱ ተዘጋጅተዋል።

የተከላው ሂደት ሳይንሳዊ እና የተደራጀ ይሆን ዘንድም በክልሉ በአጠቃላይ 1 ሺህ 345 ቦታዎች በጂኦ-ሎኬሽን መለየታቸው ታውቋል።

በትዕግስቱ ቡቼ

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: