በአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት ቀዳሚ ከሚባሉት የሀገራችን አካባቢዎች አንዱ የሆነው የሶማሌ ክልል፣ ይህንን ተፈጥሯዊ ፈተና ለመቀልበስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል።
ባለፉት ዓመታት በተተገበሩት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብሮች አበረታች ለውጦችን ያስመዘገበው ክልሉ፣ አሁን ደግሞ በአንድ ጀምበር በርካታ ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቋል።
ለዚህ ታሪካዊ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ በክልሉ በሚገኙ 11 ዞኖች ውስጥ 91 የችግኝ መትከያ ቦታዎች መዘጋጀታቸው ተገልጿል፡፡
በዚህ የአንድ ጀምበር ብሔራዊ ንቅናቄም ከአንድ ሺህ ሔክታር በላይ መሬት በተለያዩ የችግኝ ዝርያዎች እንደሚሸፈን ታቅዷል።
ይህ እርምጃ ክልሉ በረሃማነትን ለመከላከል፣ ሥነ-ምህዳሩን መልሶ ለመገንባት እና የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመረውን ጉዞ ይበልጥ እንደሚያፋጥነው ታምኖበታል።
በአዝመራው ሞሴ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: