Search

አረንጓዴ ዐሻራ፦ የተፈጥሮን ሚዛን ለመጠበቅ የኢትዮጵያ ተምሳሌታዊ እርምጃ!

እሑድ ሐምሌ 26, 2018 77

የአየር ንብረት መዛባት የደቀነው ዘርፈ ብዙ አደጋ፣ ሀገራት ነገን -ተገማች በሆነ ከፍተኛ ስጋት እንዲጠባበቁ አድርጓቸዋል።

የችግሩን አሳሳቢነት የሚመጥኑ የመፍትሔ እርምጃዎችም እየተወሰዱ እንዳልሆነ ሲነገር ይሰማል።

የአየር ንብረት ለውጥን በተመለከተ ምክክር በሚደረግባቸው ታላላቅ ጉባኤዎችም ሀገራት አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ጣት የሚቀሳሰሩበት ሁኔታ በስፋት ይስተዋላል።

አዳጊ ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን ችግሮች ለመቋቋም የሚያግዝ የቴክኖሎጂ አቅምም ስላልገነቡ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ቢሆኑም፣ ያደጉ ሀገራትም ከተፈጥሮ ቅጣት ማምለጥ እንደማይችሉ በተለያዩ አሳዛኝ እና አስፈሪ ተፈጥሯዊ ክስተቶች እየተስተዋለ ያለ ሐቅ ነው።

በከፍተኛ የሙቀት መጠን መጨመር፣ በጎርፍ መጥለቅለቅ፣ በበረሃማነት መስፋፋት፣ በሰደድ እሳት በብዙ ሀገራት ከፍተኛ ውድመት እየደረሰ መሆኑ ተጠቃሽ ናቸው።

የአየር ንብረት መዘዝ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናም እያስከተለ የሚገኘው የድርቅ አደጋ ምርታማነትን በእጅጉ እየፈተነው ሲሆን፣ በእንስሳት ላይ በደቀነው የሕልውና አደጋ የአርብቶ አደሩን ሕይወትም ማመሰቃቀሉ አልቀረም።

በመላው ዓለም እያጋጠሙ የሚገኙት የተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች መንሥኤው፣ ተፈጥሮን ከመንከባከብ አኳያ የመንግሥታት የትኩረት ማነስ እና የትውልዱ ቸልተኝነት ውጤት መሆኑን የአየር ንብረት ተቆርቋሪዎች በተደጋጋሚ ሲያሳስቡ ይደመጣል።

የአየር ንብረት መዛባትን ለመቀነስ ዓይነተኛ መፍትሔ ተደርጎ የሚወሰደው የካርቦን ልቀትን መቀነስ ነው።

ኢትዮጵያም የታዳሽ ኃይል አማራጭን በማስፋት በቁርጠኝነት ተግባራዊ እያደረገች ሲሆን፣ በምትወስዳቸው ተግባራዊ እርምጃዎች ተጽዕኖ የማሳደር አቅሟን አሳድጋለች።

ሀገራችን 2011 . መተግበር በጀመረችው እና በየዓመቱ ተጠናክሮ በቀጠለው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ፣ በሕዝቦቿ ብርቱ ርብርብ 48 ቢሊዮን ችግኞችን መትከሏም ለሀገራት ተግባር ተኮር ትምህርት ነው።

በታዳሽ ኃይል አቅርቦት ቀጣናውን ለማስተሣሠር ከጀመረቻቸው ተስፋ ሰጪ ጥረቶች በተጨማሪ ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ችግኞችን በማጋራት ዘላቂነት ላለው የጋራ ዕድገት ጽኑ መሠረት እየጣለች ትገኛለች።

በብርሃኑ አምኃ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: