Search

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ1ሺህ 672 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ማክሰኞ ሐምሌ 28, 2018 52

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 8 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 670 ወንዶች እና1 ሴት እንዲሁም 1 ጨቅላ ህፃን ሲሆን ከተመላሾች መካከል እድሜያቸው 18 ዓመት በታች የሆኑ 34 ታዳጊዎች ይገኙበታል።

መስከረም 5/ 2018 . በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 90 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ፣ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን ለማበረታታት የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

በተለያዩ ጊዜያትም ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: