በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት፣ ዩጂን ከተማ ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 3/2018 ዓ.ም በሚካሄደው 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ወደ ውድድሩ ስፍራ ደርሷል።
ሻምፒዮናው በታዋቂው ሄይዋርድ ፊልድ ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን፣ ይህ ስታዲየም በርካታ ዓለም አቀፍ ውድድሮችንና ታሪካዊ የአትሌቲክስ ሁነቶችን ያስተናገደ ስታዲየም ነው።
በዘንድሮው የዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ5000 ሜትር፣ 3000 ሜትር፣ 1500 ሜትር፣ 800 ሜትር (በሁለቱም ፆታዎች)፣ 3000 ሜትር መሰናክል (በሴቶች)፣ 400 ሜትር (በሴቶች) እንዲሁም በርምጃ ውድድር (በሁለቱም ፆታዎች) ትሳተፋለች።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: