ማንኛውም አካል የሀሳብ ልዩነቶች እና ፍላጎቱን ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ በማምጣት ሊመካከር ይገባል ሲሉ በወላይታ ዞን የጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ገልፀዋል ።
የዛሬው ትውልድ ፍላጎት ጦርነት ሳይሆን ሰላም፣ አንድነት እና እድገት በመሆኑ ማንኛውም ችግር በሀገራዊ ምክክር ብቻ መፈታት እንዳለበት ነዋሪዎች ጠይቀዋል ።
ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት በምክክር የማይፈታ የትኛውም ዓይነት ውስብስብ ችግር የለም፣ እያንዳንዱ አካል ልዩነቶቹንና የተለያየ ፍላጎቱን በውይይት ጠረጴዛ ዙሪያ በማስቀመጥ ምክክርን ብቸኛ አማራጭ አድርጎ መውሰድ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
"የዛሬው ትውልድ ኃላፊነት በመመካከርና በሰላም በመኖር የተረጋጋችና የበለጸገች ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ ማስረከብ ነው" ያሉት ነዋሪዎቹ፣ ይህንንም ለማሳካት ህብረተሰቡ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህልና እውቀቱን ማሳደግ እንዳለበት አሳስበዋል።
በሀገራችን የሚነሱ ማንኛቸውም አለመግባባቶችና ጥያቄዎች በሀገራዊ ምክክር አማካኝነት ዘላቂ እፎይታ ሊያገኙ እንደሚችሉ በመጠቆም፣ ህዝቡ በተደራጀ መንገድ የሰላምና የውይይት ባህልን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተዋል።
ለሀገር እታገላለሁ የሚል በሀገር ጉዳይ ላይ ተመካክሮ መወሰን አለበት ያሉት ነዋሪዎች መመካከርን ባህል በማድረግ ጥላቻን ማስወገድ የሁልጊዜ ተግባራችን ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በሀገራችን እየተካሄደ የምክክር መድረክ ለሀገራችን ቀጣይ እጣፈንታ ወሳኝ ምዕራፍ ይሆናል ያሉት ነዋሪዎች የዛሬ ትውልድ ሰላም በመመካከር እንደሚፀና ሊያውቁ ይገባል ብለዋል።
በትዕግስቱ ቡቼ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: