Search

የኑክሌየር ተቋማት ጣቢያ ረቂቅ ደንብ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

ማክሰኞ ሐምሌ 28, 2018 44

የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለሥልጣን በኑክሌየር ተቋማት ጣቢያ ግምገማ ረቂቅ ደንብ ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

የመደመር መንግሥት ኑክሌየርን ለሰላማዊ ልማት ለመጠቀም የተለያዩ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፉ አቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ በማሳወቅ የኑክሌየር ኮሚሽን አቋቁማ ኑክሌየርን ለኃይል እና ለተለያዩ ተግባራት ለመጠቀም እንቅስቃሴ ጀምራለች።

ይህንን ተከትሎ ልማቱ በአካባቢ እና በሰው ሕይወት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የኑክሌየር ተቋማት ጣቢያ ግምገማ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ውይይት እየተካሄደበት ነው።

በውይይቱ ላይ በርካታ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በረቂቅ ደንቡ ላይ የተለያዩ ሃሳቦች እንደሚነሱ እና ረቂቁን ለማዳበር ግብአት እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

በመሐመድ ራህመቶ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: