Search

ለስልታዊ ቡድኖች የሚቀርቡ አጀንዳዎች እየተጠናቀቁ ነው

ማክሰኞ ሐምሌ 28, 2018 42

አስር አባላት ባሏቸው 400 ጥቃቅን ቡድኖች እንዲሁም 50 አባላት ባሏቸው 80 ቡድኖች የተነሱ የአጀንዳ ሃሳቦች 25 አባላት ባሏቸው 16 የቃለጉባኤ አጠናቃሪ ቡድኖች ተጠናቅረው 250 አባላት ላሏቸው 16 ስልታዊ ቡድኖች መቅረባቸው ይታወሳል፡፡

የተጠናቀረውን ቃለጉባኤ ያዳመጡ ባለ 250 አባላት ስልታዊ ቡድኖች አልተካተቱም፣ በተነሳው ልክ አልተብራሩም ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተው ቃለ ጉባኤው እንዲሻሻል አድርገዋል፡፡

በትላንትናው የሀገራዊ ምክክር ገባኤ ውሎ ደግሞ የባለሙያዎች ስብስብ (Panel of experts) 500 አባላት ለተደራጁ 8 የአጀንዳ ቡድኖች ባለፉት ቀናት በተደረጉት የምክክር ሂደቶች በተነሱ ፅንሰ ሃሳቦች፣ ግልፅ ባልሆኑ ጉዳዮች እንዲሁም በተለያየ ረገድ ፅንፍ በያዙ አስተሳሰቦች ዙሪያ ገለፃ በማድረግ ለቃለ ጉባኤዎቹ መዳበር የሚያግዙ ሀሳቦችን አቅርበዋል፡፡

የስልታዊ ቡድን የአጀንዳ ሃሳቦችን በቃለ ጉባኤ የሚያጠናቅሩ የባለ 25 አባላት አጠናቃሪ ቡድኖችም ከትላንት ከሰዓት እስከ ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ የቀረቡ ሳይንሳዊ ማብራሪያዎችን እና ገለፃዎችን ተከትሎ ያጠናከሩትን ሃሳብ እንደገና ሲያዳብሩ ውለዋል፡፡

ይህ የዳበረ ቃለ ጉባኤ ዛሬ ከሰዓት በሚኖረው የምክክር ውሎ 250 አባላት ላሏቸው 16 ስልታዊ ቡድኖች የሚቀርብ ይሆናል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: