የኢትዮጵያ ወጣቶች በዚህ የክረምት ወቅት በነጻ በቀረበው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ የስልጠና መርኃ ግብር ላይ እንዲሳተፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ወጣቶች ባስተላለፉት መልእክት፣ ይህ ክረምት በከንቱ እንዲያልፍ ሊፈቀድለት የማይገባ ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል ብለዋል።
የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኮርሶች በነጻ የሚገኙ መሆናቸውን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሚሰጠው የምስክር ወረቀትም ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው መሆኑን ገልፀዋል።
5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ቀድመው ወስነዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ ነው ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወጣቶች በዚህ የስልጠና መርኃ ግብር ላይ ለመሳተፍ በ ethiocoders.et ላይ መምዘገብ እንደሚችሉም ተመላክቷል፡፡
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: