Search

ከ56 ሺህ ቶን በላይ የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ቀርቧል:- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል

Aug 18, 2025

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዘንድሮው ዓመት ከ56 ሺህ ቶን በላይ የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
በዚሁ ዘርፍ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
በክልሉ የቅመማ ቅመም ሰብሎች በስፋት ከሚመረትባቸው አካባቢዎች አንዱ የሸካ ዞን ነው።
በዞኑ የኪ ወረዳ ህብረት ፍሬ ቀበሌ ከ400 ሄክታር በላይ በሆነ ማሳ ላይ እርድ እየተመረተ ይገኛል።
በቀበሌው "ይቢ" ተብሎ በሚጠራው መንደር የሚገኙ 63 አርሶአደሮች ምርቱን በኩታ ገጠም የእርሻ ዘዴ በማልማት ተጠቃሚ በመሆን ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በክልሉ ከ56 ሺህ ቶን በላይ የተለያዩ የቅመማ ቅመም ምርቶች ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን ተናግረዋል።
 
በሰለሞን ባረና