Search

በጅማ ዞን ከ3 ሺህ 300 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የሱፍ ምርት በኩታ ገጠም እየለማ ነው

ቅዳሜ ነሐሴ 02, 2018 90

በጅማ ዞን የግብርናውን ሥራ በማዘመን በዘርፉ እንደ ሀገር የተያዘውን ግብ ለማሳካት በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም በዞኑ በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ 3 ሺህ 300 ሄክታር በላይ መሬት ላይ የሱፍ ምርት በኩታ ገጠም (ክላስተር) እየተመረተ ይገኛል።

እየተከናወነ ባለው ሰፊ የግብርና ሥራም አበረታች ውጤቶች እየተመዘገበ ነው።

በቀጣይም የሱፍ ምርታማነትን ይበልጥ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ መሆኑ ታውቋል።

በወሰኑ አውግቸው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: