ስማቸው ከወላይታ ሕዝብ ታሪክ ጋር የሚነሣው የሀገር ሽማግሌ እና አንጋፋ የታሪክ ተመራማሪ የነበሩት አቶ አብራሃም ባቾሬ በገጠማቸው የጤና እክል በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
በወላይታ ሕዝብ ዘንድ እጅግ የተከበሩ የነበሩት አቶ አብረሃም፣ በኢትዮጵያ በመንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በተለያዩ ኃላፊነት ሀገርን እና ሕዝብን አገልግለዋል።
በኢትዮጵያ አየር ኃይል፣ በዓለም አቀፍ የሕፃናት ድርጅት፣ በወላይታ ልማት ማኅበር፣ በወላይታ ዞን ባሕል ቱሪዝም፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባነት እና በተለያዩ የሥራ መስኮች በኃላፊነት እና በባለሙያነት ሠርተዋል።
አቶ አብራሃም ባቾሬ የወላይታ ታሪክ በዓለም እንዲታወቅ የተለያዩ የጥናት እና ምርምር ሥራዎችን የሠሩ ሲሆን፣ በተለይ የወላይታ ዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓለም ቅርስነት በዩኔስኮ እንዲመዘገብም ከፍተኛ ሚናቸውን ተወጥተዋል።
አቶ አብራሃም ባቾሬ የወላይታ ሀገር ሽማግሌ ሆነውም የወላይታ አካባቢው እና ሀገራዊ ጉዳዮች በሰላማዊ መንገድ በመፍታት እና አስታራቂ በመሆን ያገለገሉ የሰላም አምባሳደርም ነበሩ።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በአቶ አብራሃም ባቾሬ ኅልፈተ ሕይወት የተሰማውን ኀዘን እየገለጸ ለወዳጅ ዘመድ መጽናናትን ይመኛል።
በትዕግሥቱ ቡቼ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: