በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ቁንቢ ወረዳ ስር በሚገኙት ሀሮሪ እና ሀሮ ጉራቲ ቀበሌዎች የተገነቡ ሁለት የሶላር ወይም የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
እነዚህ በ640 ሚሊዮን ብር ከፍተኛ በጀት የተሰሩት የንፁህ ኢነርጂ ማመንጫዎች፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ጥያቄ በዘላቂነት የሚመልሱ ናቸው።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ ኢንጂነር ሱልጣን ወሊን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የክልል እና የዞን የሥራ ኃላፊዎች ፕሮጀክቶቹን ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
አጠቃላይ 850 ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው እነዚህ ፕሮጀክቶች፣ 3 ሺህ 646 ለሚሆኑ አባዎራዎች አስተማማኝ የብርሃንና የኃይል ምንጭ በመሆን የአካባቢውን ነዋሪ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ይሆናሉ።
ይህ ስኬት መንግሥት የንፁህ ኢነርጂ አቅርቦትን በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በማዳረስ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት የጀመረውን ሀገራዊ ሥራ በተጨባጭ የሚያሳይ ነው።
በቴዎድሮስ ታደሰ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: