የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በ2ኛ ዙር የሰለጠኑ 864 የፖሊስ መኮንኖችን አስመርቀዋል።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው፣ ለተመራቂ የፖሊስ መኮንኖች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ተመራቂዎቹ በንድፈ ሐሳብ እና በተግባር በጠንካራ ዲሲፕሊን ሥልጠናቸውን በብቃት ያጠናቀቁ፣ በአካልና በመንፈስ ጠንክረው የወጡ በመሆናቸው በፖሊስ መኮንንነት ማዕረግ ተመርቀዋልም ነው ያሉት።
ተመራቂዎች በቆይታችሁ ያገኛችሁት እውቀት ለላቀ ፖሊሳዊ ስብዕና የሚያበቃችሁ እንደመሆኑ ወደ ሥራ ስትሰማሩም ያለአድልዎና ልዩነት በታማኝነት፣ በጀግንነት፣ በሰብዓዊነትና በክብር፣ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እንደምታገለግሉ ሙሉ እምነት አለኝ ሲሉም አክለዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: