የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ምክረ-ሀሳቦችን ወጥ በሆነና በጥራት በተደራጀ መልኩ ለማዘጋጀት የሚያስችለውን ስራ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል።
ቀደም ሲል ስምንቱ ባለ 500 አባላት ቡድኖች ያዘጋጇቸውንና የተስማሙባቸውን ምክረ-ሀሳቦች እንዲያናብብ፣ እንዲያጣጥም እና እንዲያደራጅ 120 አባላት ያሉት ቡድን ተቋቁሞ ስራውን ሲያከናውን መቆየቱ እና በትላንትናው ዕለት ውጤቱን ማቅረቡ ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት ደግሞ ከዚሁ 120 አባላት ካሉት ቡድን የተመረጡ 34 አባላት በስምንት ንኡስ ቡድኖች ተከፋፍለው የእያንዳንዱን አጀንዳ ሃሳቦች በጥልቀት ሲመረምሩ ውለዋል።
አባላቱ በተለያዩ አጀንዳዎች ስር በተደጋጋሚ የተነሱ ሃሳቦች እንዳይኖሩ የመለየት፣ ያለ ምድባቸው የተነሱ ሃሳቦችን ወደሚመለከታቸው የአጀንዳ ምድብ የመመለስ፣ እንዲሁም የማጥራትና የማጣጣም ስራዎችን በዝርዝር በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ይህ ሰፊ ስራ የሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ምክረ-ሀሳቦችን ወጥ በሆነና ጥራት ባለው መልኩ ለማደራጀት የሚያግዝ ሲሆን፤ ሂደቱ እስከ ነገ የሚቀጥል መሆኑን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: