Search

የጋምቤላ ክልል ከ 7 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ገቢ አድርጓል - ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ

ሰኞ ነሐሴ 11, 2018 66

የጋምቤላ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 7 ሺህ 98 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረጉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሯ ይህንን የገለጹት በጋምቤላ ከተማ በማካሄድ ላይ በሚገኘው የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የክልሉን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው።

ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ ባቀረቡት ሪፖርት፤ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር ተፈትቶ አስተማማኝ ሰላም በመፈጠሩ የተስተጓጎሉ የልማት ስራዎችን በማስቀጠል አፈጻጸማቸውን ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።

በተለይም በግብርና፣ በማዕድን፣ በኢንቨስትመንት እና በሌሎች ቁልፍ ዘርፎች ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሯ፣ ሕገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ዝውውርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት 7 ሺህ 98 ኪሎ ግራም ወርቅ ወደ ብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረግ መቻሉን እንደ ማሳያ አቅርበዋል።

ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ1 ሺህ 669 ኪሎ ግራም ብልጫ እንዳለው አብራርተዋል።

በክልሉ ቀጣይነት ያለው ሰላምና ልማትን በማረጋገጥ የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እውን ለማድረግ የተጀመሩ ስኬታማ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስፋትና የታዩ ውስንነቶችን በማረም፣ በአዲሱ የበጀት ዓመት የተሻለ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማስመዝገብ የክልሉ መንግስት ዋና የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሯ አፅንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

 

በሚፍታህ አብዱልቃድር

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: