Search

የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ኤግዚቢሽን በጅማ

ማክሰኞ ነሐሴ 13, 2017 150

የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ኤግዚቢሽን በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በጅማ ዞን ለግብርና ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ የግብርና ምርቶችን ለማምረት መቻሉን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ኤግዚቢሽኑን በከፈቱበት ወቅት አስታውቀዋል።
በዞኑ የተመረቱ የግብርና ምርቶች ለሃገር ውስጥ ፈጆታ አልፈው ለውጭ ገበያ እየቀረቡ መሆኑንም ተናግረዋል።
በኤግዚቢሽኑ ጅማ እና አካባቢዋ የሚመረቱ የግብርና ውጤቶች፣ የኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲሁም የባሕል አልባሳት እና በእጅ የተቀረፁ ቅርፃ ቅርፆች ለገበያ ቀርበዋል።
ኤግዚቢሽኑ በጅማ ዞን እና በከተማው ንግድ ፅሕፈት ቤት ቅንጅት የተዘጋጀ ሲሆን ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
ራሄል አብደላ