Search

"በብልፅግና ዘመን የመሠረት ድንጋይ አስቀምጦ መጥፋት፤ ... አዘግይቶ ሀብት ማባከን አይፈቀድም"፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

Aug 19, 2025

የሚኤሶ - ድሬዳዋ የፍጥነት መንገድ መንግሥት ትራንስፖርትን ለማዘመን ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፍጥነት መንገዱን ዛሬ በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት ባስተለላፉት መልዕክት፥ ፕሮጀክቱ "የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተያዘው ራዕያችን እውን እየሆነ መምጣቱን ያሳያል" ብለዋል።

መንገዱ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ከሁለት ክልሎች ጋር የሚያስተሳስር በመሆኑ በክልሎች መካከል ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መስተጋብር ለማጎልበት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም ገልፀዋል።

የፍጥነት መንገዱ የተሳለጠ የትራንስፖርት አማራጭ እንዲኖር ለማድረግ፣ የሎጂስቲክስ ወጪን ለመቀነስ፣ የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ አጋዥ መሆኑንም አንስተዋል።

"በብልፅግና ዘመን፣ በብልፅግና ባህልና ምግባር የመሠረት ድንጋይ አስቀምጦ መጥፋት፤ ጀምሮ መተው፤ ከጥራት በታች ሠርቶ መመረቅ፤ አዘግይቶ የሀገር ሀብትን ማባከን ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ አይፈቀድም" ብለዋል።

የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣትና የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል በመንገድ መሠረተ-ልማት ላይ ኢንቨስት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ያላሰለሰ ክትትል እንደሚደረግም አረጋግጠዋል።

በላሉ ኢታላ

#ኢቢሲዶትስትሪም #ሚኤሶ_ድሬዳዋ #ፍጥነት_መንገድ