ከሰሞኑ የኢፌዴሪ መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሀገር ዐቅም የሚፈቅደውን ርምጃ እየወሰደ መሆኑን ተከትሎ ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መወሰኑን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ማስታወቁ ይታወሳል።
ይህንን መረጃ ተከትሎ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገፆች “የተፈቀደው አዲሱ የደመወዝ ስኬል ይህ ይመስላል” የሚሉ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተዘዋወሩ እና በርካቶችን እያሳሳቱ መሆኑን ተመልክተናል።
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) እነዚህን “የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ስኬል” በሚል በአንዳንድ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚናፈሱ አሳሳች መረጃዎች እንድትተዋቸው በሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የመንግስት ደምወዝን አስመልክቶ ትክክኛውን መረጃ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አማካይነት ብቻ የሚወጣ መሆኑን መገንዘብ እንደሚያስፈልግም ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።
በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የሚዘዋወሩ እና ምንጫቸው ያልታወቀ ሀሰተኛ መረጃዎችን ከማጋራታችን በፊት መረጃዎችን በጥንቃቄ መከታተል እና ትክክለኛውን መረጃ ከምንጩ በማጣራት ማረጋገጥ የሁልግዜ ተግባራችን ሊሆን እይገባል።