Search

ፓኪስታን የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና እንድትመረጥ ኢትዮጵያ ላደረገችው ድጋፍ አመሰገነች

ረቡዕ ነሐሴ 14, 2017 95

ፓኪስታን ከወራት በፊት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅ የፀጥታው  ክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና እንድትመረጥ ኢትዮጵያ ላደረገችው ድጋፍ አመሰገነች።

የፓኪስታን የላይኛው ክር ቤት ሴኔት መሪ እና የቀድሞ  የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዩሱፍ ራዛ ጌላኒ በአረንጓዴ አሻራ ላይ ውይይት ለማድረግ ወደ ሀገሪቱ ያቀናውን የኢትይጵያ ወጣቶች ዑካን ቡድን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር በሀገር ውስጥ የተገኘውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ውጤታማ ተሞክሮ ለማጋራት የልዑካን ቡድኑ ወደ ሀገራቸው በመምጣቱ የኢትዮጵያ መንግስትን አመስግነዋል።

በተያዘው ዓመት ፓኪስታን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅ የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል እንድትሆን ኢትዮጵያ ያሳየችው ድጋፍ ሀገራቱ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች የሚያደርጉትን የትብብር አድማስ የሚያሰፋ ስለመሆኑ የሴነቱ መሪ አንስተዋል።

ፓኪስታን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ትብብር በአፍሪካ ደረጃ እንዲያድግ ጭምር ስትራቴጂያዊ አድርጋ እንደምትወስደውም የሴኔቱ መሪ ዩሱፍ ራዛ ጌላኒ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የፓኪስታን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጀማል በከር ( /ር) ኢትዮጵያ የፊታችን ጳጉሜን በምታሰናዳው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ላይ ፓኪስታን እንድትሳተፍ ጋብዛዋል።

ሁለቱ ሀገራት የጀመሩትን ግንኙነት ለማሳደግ ጽኑ ፍላጎት መኖሩን የገለጹት አምባሳደር ጀማል፤ የፓኪስታኑ ፕሬዚዳንት አሲፍ አሊ ዛርዳሪ ኢትዮጵያን እንደሚጓበኙም  አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ የወጣቶቹ ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ ተሞክሮ ከማካፈል ባሻገር በፓኪስታን የሴኔት  ስብሰባ ላይ በመገኘት  የልምድ ልውውጥ አድርጓል፡፡

በሰዒድ ዓለሙ