Search

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጉዞ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ ጀምሯል፦ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

እሑድ ነሐሴ 17, 2018 65

የትምህርት ሚኒስቴር 2018 . 12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ይፋ ባደረገበት መግለጫ፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በትምህርት ዘርፉ ላይ የተተገበሩ የሪፎርም እርምጃዎች ተስፋ ሰጪ ለውጦችን እያመጡ መሆኑን አስታውቋል።

የሪፎርሙ ዋና ትኩረት በቁጥር መብዛት ላይ ሳይሆን፣ በብቃትና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ትውልድ መፍጠር መሆኑን የገለጹት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የዘንድሮው ውጤት የዚሁ እቅድ ነጸብራቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለፈው ዓመት አንድም ተማሪ ያላሳለፉ (ዜሮ ውጤት ያስመዘገቡ) ትምህርት ቤቶች ቁጥር 1 ሺህ 232 የነበረ ሲሆን፣ ዘንድሮ ይህ ቁጥር ወደ 565 ዝቅ ማለቱ 700 በላይ ትምህርት ቤቶች ከነበሩበት የውድቀት አዙሪት ወጥተው ተማሪዎቻቸውን ማሳለፍ መጀመራቸውን ጠቁመዋል።

በተቃራኒው ደግሞ ሁሉንም ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉ የጥራት ተምሳሌት ትምህርት ቤቶች ቁጥር 62 ወደ 88 አድጓል ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም ተማሪዎች የማይሳካላቸው ችሎታ ስለሌላቸው ሳይሆን፣ የሚሰጣቸው የትምህርት ድጋፍና ግብዓት ልዩነት ስላለው ነው በማለት የትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ ስራ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያን የወደፊት ተስፋ ለማሳካት የአዳሪ ትምህርት ቤቶች ሚና የጎላ በመሆኑ፣ ቁጥራቸውን 5 ወደ 9 በማሳደግ ዘንድሮ 2 ሺህ 500 አዳዲስ ኤሊት ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት ተጠናቅቋል።

በተጨማሪም ሚኒስቴሩ ከሰዎች ለሰዎች (Menschen for Menschen) ድርጅት ጋር በመተባበር 35 ግዙፍ የሞዴል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እየገነባ ይገኛል።

እነዚህ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከአካዳሚክ ትምህርት ጎን ለጎን በተግባራዊ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እንዲታነጹ በማድረግ እንዲሁም ወደ ስራ ዓለም ሊያስገባቸው የሚችል በቂ የሙያ ክህሎት ኖሯቸው እንዲወጡ ያስችላቸዋል።

በላሉ ኢታላ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: