የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በክልሉ የ2019 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) በአዳማ ከተማ በሚገኘው ገዳ ኪሎሌ ትምህርት ቤት በመገኘት የመማር ማስተማር ሥራውን አስጀምረዋል።
ኃላፊው መምህራን ባላቸው ዕውቀት ጥራት ያለው ትምህርት እንዲሰጡ፣ ወላጆች የልጆቻቸውን ትምህርት በቅርበት እንዲከታተሉ እንዲሁም ተማሪዎች ጥሩ ውጤት ለማምጣት ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲያጠኑ አሳስበዋል።
በ2019 የትምህርት ዘመን 13 ሚሊዮን 500 ሺህ ተማሪዎችን ለማስተማር ታቅዶ እስካሁን 7 ሚሊዮን ተማሪዎች መመዝገባቸውን ዶ/ር ቶላ ጠቁመዋል።
ከሚቀጥለው እሁድ በኋላ ምንም ዓይነት ምዝገባ እንደማይኖር አስታውሰው፣ ወላጆች ያልተመዘገቡ ልጆቻቸውን በፍጥነት በማስመዝገብ ትምህርት ማስጀመር እንዳለባቸው ጥሪ ማቅረባቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: