Search

በአፍሪካ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ከፍተኛ አጀንዳ እየሆነ መጥቷል፦ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር)

ቅዳሜ ነሐሴ 17, 2017 41

በተለያዩ ጊዜያት በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር የተጠረጠሩ ሰዎች ከበርካታ ሚሊየን ብሮች ጋር በኢትዮጵያ ተይዘዋል።

ይህ ችግር የአብዛኛው አፍሪካውያን ሀገራት የራስ ምታት መሆኑን እና ጉዳዩ ከፍተኛ አጀንዳ እየሆነ መምጣቱን የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ይገልጻሉ።

አፍሪካ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት በ10 ዓመት ውስጥ እስከ 1 ትሪሊየን ዶላር እንደምታጣ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አስረድተዋል።

 በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር  የሚገኝ ገንዘብ ለሽብርና ለተለያዩ አላማዎች ስለሚውል ጥንቃቄ የቅድሚያ ርምጃ ሊሆን እንደሚገባም የኢኮኖሚ ባለሙያው ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

የፋይናንስ ደህንነት በመቆጣጠር ረገድ በተለይ ተቋማትን እና በዘርፉ ያለውን እውቀት ማጠናከር እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

ግለሰቦችም ለፋይናስ ስጋት ተጋላጭ እንዳይሆኑ ከየትኛውም መተግበሪያ ሆነ በሌሎች መንገዶች የሚደረጉ የገንዘብ ዝውውሮችን  ተጠንቅቀው ማከናወን እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ሚዲያው ማህበረሰቡን ከማንቃት  እና ወንጀ ሎችን በማጋለጥ ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለበትም አንስተዋል።

ኢትዮጵያ የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ግብረ ኃይል ስብሰባ ን ማስተናገዷ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ከመቅረፍ አኳያ አንድምታው ላቅ ያለ እንደሆነም ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

 

በሜሮን ንብረት

#EBC #ebcdotstream #Economy #money