በአፋር ክልል በመሰረታዊ የፍጆታ ምርቶች ላይ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 180 የንግድ ተቋማት ላይ ርምጃ መወሰዱን የክልሉ ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ አስታውቋል።
የቢሮው የንግድ ቁጥጥር እና ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዶ አሊ ለኢቢሲ እንደተናገሩት የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች ንግድ ላይ በተከናወነው የቁጥጥር ሥራ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪያደረጉ 180 ንግድ ቤቶች እንዲታሸጉ ተደርጓል።
በክልሉ 27 ትላልቅ የእሁድ ገበያዎች ላይ ሕጋዊ የንግድ ስርዓት እንዲኖር የቁጥጥር ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ አቶ አብዶ አሊ ተናግረዋል።
በገበያ ማዕከላት እና ንግድ ቤቶች ላይ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር የቁጥጥር ሥራው እስከ ታችኛው መዋቅር መዘረጋቱን እና ሕብረተሰቡ ሕገ ወጥ ነጋዴዎችን ሲመለከት ጥቆማ እንዲሰጥ የግንዛቤ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛል ብለዋል።
አላስፈላጊ ዋጋ ጭማሪ እና ምርት በማከማቸት የገበያ አለመረጋጋትን እንዲፈጠር በሚያደርጉ ነጋዴዎች ሕጋዊ እርምጃው ተጠናክረው እንደሚቀጥል ተገልጿል ።
በሁሴን ሞሐመድ