ኢትዮጵያ እያመረተች ነው እኛም የኢትዮጵያን እንግዛ ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ መልዕክት አስተላለፉ።
ርዕሠ መስተዳድሩ ይህን ያሉት የሲዳማ ክልል የንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ከክልሉ ንግድ ዘረፍ ማኀበራት ም/ቤት ጋር “የኢትዮጵያን ይግዙ” በሚል መሪ ሀሳብ ያዘጋጁት ኤግዚቢሽን እና ባዛር የማስጀመርያ መርሀ-ግብር ላይ ነው።
ሲዳማ ክልልን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ ብሎም በክልሉ የሚመረተውን ምርት ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ሲሉም ርዕሠ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
ባለሀብቶን በማምረቻው ዘርፍ በስፋት በማሰማራት የወጪ ንግድን ለማጠናከር ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል።
በተለይም ምርቶችን ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የንግድ ሚዛንን ለማስጠበቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በፈቃደአብ አለማየሁ
#EBC #ebcdotstream #Hawassa #Madeinethiopia