የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ለአንድ ክፍለ ዘመን ተኩል ገደማ የሀገራችንን ሉዓላዊነት፣ የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት ለማስጠበቅ በፅናት የቆመ የኢትዮጵያ የማይበገር ጋሻና መከታ ነው።
119ኛውን የመከላከያ ሠራዊት ቀን ስናከብር፣ የሀገራቸውን ጥሪ ተቀብለው ለሀገር ክብርና ለሰንደቅ ዓላማ ከፍታ ውድ ሕይወታቸውን የገበሩትን እና ዛሬም በየግንባሩ በፅናት የሚቆሙትን ጀግኖቻችንን በታላቅ አክብሮትና ኩራት እያሰብን ነው።
በተቋማዊ ማሻሻያዎች ይበልጥ የተጠናከረው፣ በዘመናዊ ትጥቅ፣ በላቀ ቴክኖሎጂና በፅኑ ወታደራዊ ስነ-ምግባር የታነፀው ሠራዊታችን፤ የሀገራችንን ሰላም አስተማማኝ በማድረግ ለልማታችንና ለከፍታችን ጉዞ ጽኑ መሠረት ሆኖ ቀጥሏል።
ለሀገር ሰላምና ሉዓላዊነት ሌሊትና ቀን ዋጋ ለሚከፍለው ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ክብርና ምስጋና ይገባል።
በፅኑ ሠራዊታችን አሸናፊነት ታላቋን ኢትዮጵያ እናስክብራለን።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: