ቅዱስ ሲኖዶሱ ጉባኤውን በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን የዛሬው በጥቅምት ወር የሚካሄደውን ምልዐተ ጉባኤ ነው።
ጉባኤውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ በብፁኡ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቃለ ምህዳ ተከፍቷል ።
ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያኗ ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በተለይም:-
በአንዳንድ አህጉረ ስብከት የሚታዩ የአሠራር ክፍተቶችን ማረም፣ የምእመናን አያያዝ እንዲሁም ሐዋርያዊ ተልእኮን በተገቢው ሁኔታ መፈጸም ላይ ውይይት ያደርግባቸዋል ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪ ቅዱስ ሲኖዶሱ በተለያዩ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይም ትኩረት ያደርጋል የተባለ ሲሆን ሰላምን ለማስፈን በሚደረግ ጥረት ሁሉ ከባለድርሻ አካላት ጋር መስራት በሚገባው ጉዳይ ላይ ውይይት የሚያደርግ ይሆናል።
ጉባዔው ብጹኣን አበው ሊቃነ ጳጳሳት: የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት በተገኙበት የተጀመረ ሲሆን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መከፈቱን ለምእመናን አብስሯል ።
በመሐሪ ዓለሙ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: